ሳምንት 3 · ቀን 14 (ሐሙስ)
📅 Meskerem 21, 2019
ኦሪት ዘፍጥረት 35, 36, 37 · መዝሙረ ዳዊት 12 · የማርቆስ ወንጌል 14
ኦሪት ዘፍጥረት
ምዕራፍ 35
1.ያዕቆብ ወደ ቤቴል ተመለሰ
1 እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሥና ወደ ቤቴል ውጣ፤ እዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ” አለው። 2.ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና ዐብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ። 3.ተነሥተን ወደ ቤቴል እንውጣ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፣ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።” 4.ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሰብስበው፣ የጆሮ ጕትቾቻቸውን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት። ያዕቆብም ወስዶ ሴኬም አጠገብ ካለው ወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። 5.ያንም ቦታ ለቅቀው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው በነበሩት ከተሞች ሁሉ ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ስለ ለቀቀባቸው የያዕቆብን ልጆች ያሳደዳቸው አልነበረም። 6.ያዕቆብና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ፣ በከነዓን ወደምትገኘው፣ ቤቴል ወደተባለችው ወደ ሎዛ ደረሱ። 7.ያዕቆብም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ ስሙን ኤል-ቤቴል አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ ሸሽቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነበር። 8.በዚህ ጊዜ የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ ሞተች፤ ከቤቴል ዝቅ ብሎ በሚገኘው ወርካ ዛፍ ሥር ተቀበረች። ከዚህ የተነሣም ያ ቦታ አሎንባኩት ተባለ። 9.ያዕቆብ ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ከተመለሰ በኋላ፣ እግዚአብሔር ለያዕቆብ ዳግመኛ ተገለጠለት፤ ባረከውም። 10.እግዚአብሔርም፣ “እስካሁን ስምህ ያዕቆብ ነበረ፤ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ነገር ግን ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህም እስራኤል ብሎ ጠራው። 11.ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ ብዛ ተባዛ፤ ሕዝብና የሕዝቦች ማኅበር ከአንተ ይወጣሉ፤ ነገሥታትም ከአብራክህ ይከፈላሉ። 12.ለአብርሃምና ለይሥሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ከአንተም በኋላ ይህችኑ ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።” 13.እግዚአብሔርም ከርሱ ጋራ ከተነጋገረበት ስፍራ ወደ ላይ ወጣ። 14.ያዕቆብም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፤ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት። 15.ያዕቆብም፣ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው።
ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦ 23.የልያ ልጆች፦
የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል፣
ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤ 24.የራሔል ልጆች፦
ዮሴፍ፣ ብንያም፤ 25.የራሔል አገልጋይ የባላ ልጆች፦
ዳን፣ ንፍታሌም፤ 26.የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦
ጋድ፣ አሴር ናቸው።
እነዚህ ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች ነበሩ። 27.ያዕቆብ አባቱ ወዳለበት ወደ መምሬ መጣ፤ አብርሃምና ይሥሐቅ የኖሩባት፣ ቂርያት አርባቅ ወይም ኬብሮን የተባለችው ቦታ ናት። 28.ይሥሐቅ መቶ ሰማንያ ዓመት ኖረ፤ 29.ይሥሐቅም አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።
1 እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሥና ወደ ቤቴል ውጣ፤ እዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ” አለው። 2.ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና ዐብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ። 3.ተነሥተን ወደ ቤቴል እንውጣ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፣ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።” 4.ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሰብስበው፣ የጆሮ ጕትቾቻቸውን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት። ያዕቆብም ወስዶ ሴኬም አጠገብ ካለው ወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። 5.ያንም ቦታ ለቅቀው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው በነበሩት ከተሞች ሁሉ ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ስለ ለቀቀባቸው የያዕቆብን ልጆች ያሳደዳቸው አልነበረም። 6.ያዕቆብና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ፣ በከነዓን ወደምትገኘው፣ ቤቴል ወደተባለችው ወደ ሎዛ ደረሱ። 7.ያዕቆብም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ ስሙን ኤል-ቤቴል አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ ሸሽቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነበር። 8.በዚህ ጊዜ የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ ሞተች፤ ከቤቴል ዝቅ ብሎ በሚገኘው ወርካ ዛፍ ሥር ተቀበረች። ከዚህ የተነሣም ያ ቦታ አሎንባኩት ተባለ። 9.ያዕቆብ ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ከተመለሰ በኋላ፣ እግዚአብሔር ለያዕቆብ ዳግመኛ ተገለጠለት፤ ባረከውም። 10.እግዚአብሔርም፣ “እስካሁን ስምህ ያዕቆብ ነበረ፤ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ነገር ግን ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህም እስራኤል ብሎ ጠራው። 11.ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ ብዛ ተባዛ፤ ሕዝብና የሕዝቦች ማኅበር ከአንተ ይወጣሉ፤ ነገሥታትም ከአብራክህ ይከፈላሉ። 12.ለአብርሃምና ለይሥሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ከአንተም በኋላ ይህችኑ ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።” 13.እግዚአብሔርም ከርሱ ጋራ ከተነጋገረበት ስፍራ ወደ ላይ ወጣ። 14.ያዕቆብም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፤ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት። 15.ያዕቆብም፣ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው።
የራሔልና የይሥሐቅ መሞት
35፥23-26 ተጓ ምብ – 1ዜና 2፥1-2
16.ከዚያም ከቤቴል ተነሥተው ሄዱ፤ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፤ ምጡም ጠናባት።
17.ምጡ አስጨንቋት ሳለ፣ አዋላጇ፣ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ሌላ ወንድ ልጅ ልትገላገይ ነው” አለቻት።
18.እርሷ ግን ሕይወቷ ልታልፍ በማጣጣር ላይ ሳለች፣ ልጇን ቤንኦኒ አለችው፤ አባቱ ግን ብንያም አለው።
19.ራሔልም ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ በቤተ ልሔም ተቀበረች።
20.ያዕቆብም በራሔል መቃብር ላይ ሐውልት አቆመ፤ እስከ ዛሬም የራሔል መቃብር ምልክት ይኸው ሐውልት ነው።
21.እስራኤልም ጕዞውን በመቀጠል ከጋዴር ወንዝ ባሻገር ድንኳኑን ተከለ።
22.እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ።ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦ 23.የልያ ልጆች፦
የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል፣
ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤ 24.የራሔል ልጆች፦
ዮሴፍ፣ ብንያም፤ 25.የራሔል አገልጋይ የባላ ልጆች፦
ዳን፣ ንፍታሌም፤ 26.የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦
ጋድ፣ አሴር ናቸው።
እነዚህ ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች ነበሩ። 27.ያዕቆብ አባቱ ወዳለበት ወደ መምሬ መጣ፤ አብርሃምና ይሥሐቅ የኖሩባት፣ ቂርያት አርባቅ ወይም ኬብሮን የተባለችው ቦታ ናት። 28.ይሥሐቅ መቶ ሰማንያ ዓመት ኖረ፤ 29.ይሥሐቅም አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።
ምዕራፍ 36
የዔሳው ዝርያዎች
36፥10-14 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥35-37
36፥20-28 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥38-42
1.ኤዶም የተባለው የዔሳው ትውልድ ይህ ነው።
2.ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የኤሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፂብዖን ልጅ ዓና የወለዳት ኦሆሊባማ፣
3.እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችው የእስማኤል ልጅ ቤሴሞት ነበሩ።
4.ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት፤ ቤሴሞት ደግሞ ራጉኤልን ወለደችለት።
5.እንደዚሁም ኦሆሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው።
6.ዔሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።
7.ብዙ ሀብት ስለ ነበራቸው ዐብረው መኖር አልቻሉም፤ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም።
8.ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።
9.በሴይር ተራራማ አገር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤
10.የዔሳው ወንዶች ስም፦የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤ 11.የኤልፋዝ ልጆች፦
ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤ 12.የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ቲምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው። 13.የራጉኤል ወንዶች ልጆች፦
ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህ ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው። 14.የፂብዖን የልጅ ልጅ፣ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦
የዑስ፣ የዕላምና ቆሬ። 15.ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤
የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦
አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣ 16.አለቃ ቆሬ፣ አለቃ ጎቶምና አለቃ አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ። 17.የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦
አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ። 18.የዔሳው ሚስት የአህሊባም ልጆች፦
አለቃ የዑስ፣ አለቃ የዕላምና፣ አለቃ ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ፣ ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። 19.እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ። 20.በዚያች ምድር ይኖሩ የነበሩ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ነበሩ፦
ሎጣን፣ ሦባል፣ ፂብዖን፣ ዓና፣ 21.ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ። 22.የሎጣን ወንዶች ልጆች፦
ሖሪና ሄማን፤ ቲምናዕ የሎጣን እኅት ነበረች። 23.የሦባል ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦
ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ሽፎና አውናም፤ 24.የፂብዖን ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦
አያ እና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፂብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው። 25.የዓና ልጆች፦
ዲሶንና የዓና ሴት ልጅ ኦሆሊባማ፤ 26.የዲሶን ወንዶች ልጆች፦
ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን እና ክራን፤ 27.የኤጽር ወንዶች ልጆች፦
ቢልሐን፣ ዛዕዋን እና ዓቃን። 28.የዲሳን ወንዶች ልጆች፦
ዑፅ እና አራን። 29.የሖሪውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦
ሎጣን፣ ሦባል፣ ፂብዖን፣ ዓና፣ 30.ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን።
እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
የኤዶም ነገሥታት
36፥31-43 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥43-54
31.በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦
32.የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ላይ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።
33.ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ።
34.ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ።
35.ሑሳም ሲሞት፣ በሞዓብ ምድር ምድያማውያንን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ። የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ።
36.ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።
37.ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኡል በምትኩ ነገሠ።
38.ሳኡል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።
39.የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማዪቱም ስም ፋዑ ነው፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን፣ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።
40.ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣ 41.ኦሆሊባማ፣ ኤላ፣ ፒኖን፣ 42.ቄናዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣ 43.መግዲኤል እና ዒራም።
እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው የኤዶም ዘሮች የነገድ አለቆች ነበሩ።
ይህም ዔሳው፣ የኤዶማውያን አባት ነው።
ምዕራፍ 37
የዮሴፍ ሕልሞች
1.ያዕቆብ አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ። 2.የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው።ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረ ጊዜ፣ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋራ የአባቱን በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር። እርሱም ስለ ወንድሞቹ ድርጊት ለአባቱ መጥፎ ወሬ ይዞለት መጣ። 3.እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለ ወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወድደው ነበር፤ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም አደረገለት። 4.ወንድሞቹም፣ አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወድደው መሆኑን ሲያዩ፣ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበትም ሊያናግሩት አልቻሉም። 5.ዮሴፍም ሕልም ዐለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት። 6.እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ ስሙኝ 7.እኛ ሁላችን በዕርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ በድንገት ተነሥታ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች ዙሪያዋን ከብበው ለእኔ ነዶ ሰገዱላት።” 8.ወንድሞቹም፣ “ለካስ በላያችን ለመንገሥ ታስባለህና! ለመሆኑ አንተ እኛን ልትገዛ!” አሉት፤ ስለ ሕልሙና ስለ ተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት። 9.እንደ ገናም ሌላ ሕልም ዐለመ፤ ለወንድሞቹም፣ “እነሆ፤ ሌላ ሕልም ዐለምሁ፤ ፀሓይና ጨረቃ፣ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ አየሁ” ብሎ ነገራቸው። 10.ሕልሙን ለአባቱና ለወንድሞቹ በነገራቸው ጊዜ፣ አባቱ “ይህ ያየኸው ሕልም ምንድን ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም በፊትህ ወደ ምድር ተጐንብሰን በርግጥ ልንሰግድልህ ነው?” ሲል ገሠጸው። 11.ወንድሞቹ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው።
ወንድሞቹ ዮሴፍን ሸጡት
12.ከዚህም በኋላ የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማሰማራት ወደ ሴኬም አካባቢ ሄዱ፤ 13.እስራኤልም ዮሴፍን “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ።” አለው።ዮሴፍም “ይሁን ዕሺ” አለው። 14.ያዕቆብም፣ “ሄደህ ወንድሞችህም፣ መንጎቹም ደኅና መሆናቸውን አይተህ ወሬያቸውን አምጣልኝ” አለው፤ ከኬብሮንም ሸለቆ ወደ ሴኬም ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣ 15.ሜዳ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲባዝን አንድ ሰው አግኝቶት “ምን እየፈለግህ ነው?” ሲል ጠየቀው። 16.ዮሴፍም፣ “ወንድሞቼን እየፈለግኋቸው ነው፤ መንጎቻቸውን የት እንዳሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህ?” አለው። 17.ሰውየውም፣ “ከዚህ ሄደዋል፤ ደግሞም፣ ‘ወደ ዶታይን እንሂድ’ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው።
ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ሄደ፣ ዶታይን አቅራቢያም አገኛቸው። 18.ወንድሞቹም ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቅ አዩት፤ ወደ ነበሩበትም ስፍራ ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ። 19.እነርሱም እንዲህ ተባባሉ፤ “ያ ሕልም ዐላሚ መጣ፤ 20.ኑ እንግደለውና ከጕድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም፣ ‘ክፉ አውሬ ነጥቆ በላው’ እንላለን፤ እስኪ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን!” 21.ሮቤል ግን ይህን ምክር ሲሰማ ከእጃቸው ሊያድነው ፈለገ፤ እንዲህም አለ፣ “ሕይወቱ በእጃችን አትለፍ፤ 22.የሰው ደም አታፍስሱ፤ እዚህ ምድረ በዳ፣ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት እንጂ እጃችሁን አታንሡበት።” ሮቤል ይህን ያለው ሕይወቱን ከእጃቸው አትርፎ ወደ አባቱ ሊመልሰው ዐስቦ ነበር። 23.ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደ ደረሰ፣ የለበሳትን በኅብረ ቀለማት ያጌጠች እጀ ጠባቡን ገፈፉት፤ 24.ይዘውም ወደ ጕድጓድ ጣሉት፤ ጕድጓዱም ውሃ የሌለበት ደረቅ ነበር። 25.ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ፤ አሻግረው ሲመለከቱም ከገለዓድ የሚመጡ እስማኤላውያን ነጋዴዎች የግመል ጓዝ አዩ። ነጋዴዎቹ ሽቱ፣ በለሳን ከርቤ በግመሎቻቸው ጭነው ወደ ግብጽ የሚወርዱ ነበሩ። 26.ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “ወንድማችንን መግደልና አሟሟቱን መደበቅ ምን ይጠቅመናል? 27.ከዚህ ይልቅ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች እንሽጠው፤ እጃችንን ግን በርሱ ላይ አናንሣ። ምንም ቢሆንኮ ወንድማችን፣ ሥጋችን ነው” ወንድሞቹም በሐሳቡ ተስማሙ። 28.የምድያም ነጋዴዎችም እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሱ፣ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ጥሬ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት። 29.ሮቤል ወደ ጕድጓዱ ተመልሶ ሲያይ፣ ዮሴፍን በማጣቱ ልብሱን በሐዘን ቀደደ። 30.ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ፣ “ብላቴናው ጕድጓድ ውስጥ የለም፤ የት አባቴ ልሂድ?” አለ። 31.ከዚያም የዮሴፍን እጀ ጠባብ ወሰዱ፤ አንድ ፍየልም ዐርደው እጀ ጠባቡን በደሙ ነከሩት። 32.በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስኪ እየው” አሉት። 33.እርሱም ልብሱን ዐውቆት፣ “ይህማ የልጄ እጀ ጠባብ ነው! ክፉ አውሬ በልቶታል፤ በርግጥም ዮሴፍ ተቦጫጭቋል” አለ። 34.ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለብሶ ስለ ልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፤ 35.ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና ባለመቻሉ “በሐዘን እንደ ተኰራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ። 36.በዚህ ጊዜ፣ የምድያም ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወስደው፣ ከፈርዖን ሹማምት አንዱ ለነበረው ለዘበኞች አለቃ፣ ለጲጥፋራ ሸጡት።
መዝሙረ ዳዊት
ምዕራፍ 12
1.ለመዘምራን አለቃ፤ በሸሚኒትየሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ደግ ሰው የለምና አንተው ድረስልኝ!
ከሰዎችም መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም። 2.እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤
በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ። 3.ሸንጋዩን ከንፈር ሁሉ፣
ነገር የምታበዛውንም ምላስ እግዚአብሔር ያጥፋ! 4.እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤
ከንፈራችን የእኛ ነው፤ ጌታችንስ ማነው?”
የሚሉ ናቸው። 5.እግዚአብሔር፣ “ስለ ችግረኞች መከራ፣
ስለ ድኾችም ጩኸት፣
አሁን እነሣለሁ፤
በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል። 6.የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤
ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣
በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው። 7.እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ትጠብቀናለህ፤
ከዚህም ትውልድ ለዘላለም ትከልለናለህ። 8.በሰዎች ዘንድ ክፋት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣
ዐመፀኞች በየአቅጣጫው በዛቻ ይዞራሉ።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ደግ ሰው የለምና አንተው ድረስልኝ!
ከሰዎችም መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም። 2.እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤
በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ። 3.ሸንጋዩን ከንፈር ሁሉ፣
ነገር የምታበዛውንም ምላስ እግዚአብሔር ያጥፋ! 4.እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤
ከንፈራችን የእኛ ነው፤ ጌታችንስ ማነው?”
የሚሉ ናቸው። 5.እግዚአብሔር፣ “ስለ ችግረኞች መከራ፣
ስለ ድኾችም ጩኸት፣
አሁን እነሣለሁ፤
በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል። 6.የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤
ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣
በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው። 7.እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ትጠብቀናለህ፤
ከዚህም ትውልድ ለዘላለም ትከልለናለህ። 8.በሰዎች ዘንድ ክፋት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣
ዐመፀኞች በየአቅጣጫው በዛቻ ይዞራሉ።
የማርቆስ ወንጌል
ምዕራፍ 14
ኢየሱስን ሽቱ የቀባችው ሴት
14፥1-11 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥2-16
14፥1-2፤ 14፥10-11 ተጓ ምብ – ሉቃ 22፥1-6
14፥3-8 ተጓ ምብ – ዮሐ 12፥1-8
1.ፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ሲቀረው፣ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ኢየሱስን የሚይዙበትና የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።
2.ሆኖም፣ “ሕዝቡ ዐመፅ እንዳያነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም” ይባባሉ ነበር።
3.እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ የተሠራ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፣ ብልቃጡንም ሰብራ ሽቱውን በራሱ ላይ አፈሰሰችው።
4.በዚያ ከነበሩት አንዳንዶቹ በድርጊቱ ተቈጥተው እንዲህ ይባባሉ ነበር፤ “ሽቱው ለምን እንደዚህ በከንቱ ይባክናል?
5.ይህ ሽቱ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ ተሸጦ፣ ገንዘቡን ለድኾች መስጠት ይቻል ነበር።” ሴትዮዋንም ነቀፏት።
6.ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ተዉአት፣ ለምን ታስቸግሯታላችሁ? መልካም ነገር አድርጋልኛለች።
7.ድኾች ምን ጊዜም ከእናንተ ጋራ ናቸው፤ በፈለጋችሁ ጊዜ ልትረዷቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ አልኖርም፤
8.እርሷ ማድረግ የምትችለውን ያህል አድርጋለች፤ ለመቃብሬ እንዲሆን ሰውነቴን አስቀድማ ቀብታለች።
9.እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በሚሰበክበት በዓለም ዙሪያ ሁሉ፣ በማንኛውም ስፍራ እርሷ ያደረገችው መታሰቢያ ሆኖ ይነገርላታል።”
10.ከዚህ በኋላ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።
11.እነርሱም ይህን ሲሰሙ ደስ አላቸው፤ ገንዘብ ሊሰጡትም ቃል ገቡለት፤ ስለዚህ እርሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።
የጌታ እራት
14፥12-26 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥17-30፤ ሉቃ 22፥7-23
14፥22-25 ተጓ ምብ – 1ቆሮ 11፥23-25
12.የፋሲካ በግ በሚታረድበት በቂጣ በዓል የመጀመሪያው ቀን፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ “የፋሲካ እራት የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።
13.እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፤ “ወደ ከተማ ሂዱ፤ እንስራ የውሃ የተሸከመ ሰው ይገናኛችኋል፤
14.ወደሚገባበት ቤትም ተከተሉት፤ የቤቱንም ጌታ፣ ‘መምህሩ፣ ከደቀ መዛሙርቴ ጋራ የፋሲካን እራት የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የትኛው ነው?’ ብሏል በሉት፤
15.እርሱም በሰገነት ላይ ተነጥፎ የተሰናዳ ሰፊ አዳራሽ ያሳያችኋል፤ እዚያ አዘጋጁልን።”
16.ደቀ መዛሙርቱም ወጥተው ወደ ከተማዪቱ ሄዱ፤ ማንኛውም ነገር ኢየሱስ እንዳላቸው ሆኖ አገኙት፤ ፋሲካውንም አሰናዱ።
17.በመሸም ጊዜ ኢየሱስ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ መጣ።
18.በማእድ ላይ ሳሉም፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከመካከላችሁ አንዱ፣ ዐብሮኝ የሚበላው እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አላቸው።
19.እነርሱም ዐዘኑ፤ እያንዳንዳቸውም፣ “እኔ እሆንን?” ይሉት ጀመር።
20.እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ፣ ከእኔ ጋራ እጁን በወጭቱ ውስጥ የሚያጠልቀው ነው።
21.የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈው ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት! ያ ሰው ሳይወለድ ቢቀር ይሻለው ነበር።”
22.ሲበሉም እንጀራ አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸውና፣ “ዕንኩ፤ ይህ ሥጋዬ ነው” አላቸው።
23.ጽዋውንም አነሣ፤ አመስግኖም ሰጣቸው፤ ሁሉም ከዚያ ጠጡ።
24.ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፤
25.እውነት እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት አዲሱን የወይን ፍሬ እስከምጠጣበት እስከዚያች ቀን ድረስ ዳግም ከወይን ፍሬ አልጠጣም።”
26.ከዚህ በኋላ መዝሙር ዘምረው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ።ጴጥሮስ እንደሚክደው ኢየሱስ አስቀድሞ ተናገረ
14፥27-31 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥31-35
27.ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ሁላችሁ ትክዱኛላችሁ፤“ ‘እረኛውን እመታለሁ በጎቹም ይበተናሉ’ 28.ከተነሣሁ በኋላ ግን፣ ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ።” 29.ጴጥሮስም፣ “ሁሉም ቢሰናከሉ እንኳ እኔ አልሰናከልም” አለ። 30.ኢየሱስም፣ “እውነት እልሃለሁ፤ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው። 31.ጴጥሮስም፣ “ከአንተ ጋራ ብሞት እንኳ ከቶ አልክድህም” በማለት ይበልጥ አጽንቶ ተናገረ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።
ኢየሱስ በጌቴሴማኒ ጸለየ
14፥32-42 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥36-46፤ ሉቃ 22፥40-46
32.ከዚህ በኋላ ጌቴሴማኒ ወደሚባል ስፍራ ሄዱ፤ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን፣ “እኔ ስጸልይ እናንተ እዚህ ተቀመጡ” አላቸው።
33.ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስንም ከርሱ ጋራ ይዞ ሄደ፤ እጅግ ያዝን ይጨነቅ ጀመር።
34.ደግሞም፣ “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ ዐዝናለች፤ እዚሁ ሁኑና ነቅታችሁ ጠብቁ” አላቸው።
35.ጥቂት ዕልፍ ብሎም በምድር ላይ በመውደቅ ቢቻል ሰዓቱ ከርሱ እንዲያልፍ ጸለየና፣
36.“አባ፣ አባት ሆይ፤ ሁሉ ነገር ይቻልሃልና ይህን ጽዋ ከእኔ አርቀው፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን” አለ።
37.ተመልሶም ሲመጣ ደቀ መዛሙርቱን ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም እንዲህ አለው፣ “ስምዖን ሆይ፤ ተኝተሃልን? አንድ ሰዓት እንኳ ነቅተህ መጠበቅ አቃተህ?
38.ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ፤ ጸልዩም፤ መንፈስ ዝግጁ ነው፣ ሥጋ ግን ደካማ ነው።”
39.እንደ ገናም ሄዶ መጀመሪያ የጸለየውን ደግሞ ጸለየ።
40.ዳግመኛም ሲመለስ ዐይናቸውን እንቅልፍ ከብዶት ተኝተው አገኛቸው፤ የሚመልሱለትንም አያውቁም ነበር።
41.ሦስተኛ ጊዜም መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም እንደ ተኛችሁና እንዳረፋችሁ ናችሁ? ይበቃል! ሰዓቲቱ ደርሳለች፤ እነሆ፤ የሰው ልጅ ለኀጢአተኞች እጅ ዐልፎ ይሰጣል!
42.ተነሡ፤ እንሂድ! እነሆ፤ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል።”
ኢየሱስ ተያዘ
14፥43-50 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥47-56፤ ሉቃ 22፥47-50፤ ዮሐ 18፥3-11
43.ወዲያው እየተናገረ ሳለ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ዐብረውትም ሰይፍና ዱላ የያዙ፣ ከካህናት አለቆች፣ ከጸሐፍትና ከሽማግሌዎች የተላኩ ብዙ ሰዎች ነበሩ።
44.አሳልፎ የሚሰጠውም፣ “እኔ የምስመው እርሱ ነውና ያዙት፤ ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት” በማለት አስቀድሞ ምልክት ሰጥቷቸው ነበር።
45.እንደ ደረሰም ወዲያው ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ!” ብሎ ሳመው፤
46.ሰዎቹም ኢየሱስን ያዙት፤ አሰሩትም።
47.በአቅራቢያው ቆመው ከነበሩት አንዱ ሰይፉን መዝዞ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ ጆሮ ቈረጠ።
48.ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እንደ ወንበዴ በሰይፍና በቈመጥ ልትይዙኝ መጣችሁን?
49.በየዕለቱም በቤተ መቅደስ እያስተማርሁ ከእናንተ ጋራ ስኖር አልያዛችሁኝም፤ መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ።”
50.በዚህ ጊዜ ሁሉም ትተዉት ሸሹ።
51.ዕርቃኑን ለመሸፈን በፍታ ያገለደመ አንድ ወጣት ኢየሱስን ይከተል ነበር። ሰዎቹም ይህን ወጣት በያዙት ጊዜ፣
52.ግልድሙን ጥሎ ዕራቍቱን ሸሸ።
ኢየሱስ በሸንጎ ፊት
14፥53-65 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥57-68፤ ዮሐ 18፥12-13፤ 18፥19-24
14፥61-63 ተጓ ምብ – ሉቃ 22፥67-71
53.ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዱት፤ በዚያም የካህናት አለቆች፣ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ሁሉ ተሰበሰቡ።
54.ጴጥሮስም ከሩቅ እየተከተለው፣ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ዘለቀ፤ በዚያም ተቀምጦ ከጠባቂዎቹ ጋራ እሳት ይሞቅ ነበር።
55.የካህናት አለቆችና ሸንጎው በሙሉ ኢየሱስን ለመግደል ምስክር ፈለጉ፤ ነገር ግን ማግኘት አልቻሉም።
56.ብዙዎች በሐሰት ቢመሰክሩበትም፣ ቃላቸው አንድ ሊሆን አልቻለም።
57.አንዳንዶቹም ተነሥተው እንዲህ ሲሉ በሐሰት መሰከሩበት፤
58.“ይህ፣ ‘የሰው እጅ የሠራውን ቤተ መቅደስ አፍርሼ፣ በሦስት ቀን ሌላ የሰው እጅ ያልሠራውን እሠራለሁ’ ሲል ሰምተነዋል።”
59.ይህም ሆኖ፣ እንኳ ምስክርነታቸው አንድ አልሆነም።
60.ሊቀ ካህናቱም ተነሥቶ በፊታቸው በመቆም፣ “እነዚህ በአንተ ላይ የሚመሰክሩት ምንድን ነው? ለምን አትመልስም?” በማለት ኢየሱስን ጠየቀው።
61.ኢየሱስ ግን ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም።ሊቀ ካህናቱም እንደ ገና፣ “የቡሩኩ ልጅ፣ ክርስቶስ አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። 62.ኢየሱስም፣ “አዎን ነኝ፤ የሰው ልጅ በኀያሉ ቀኝ ሲቀመጥ፣ በሰማይ ደመናም ሲመጣ ታዩታላችሁ” አለ። 63.ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና፣ እንዲህ አለ፤ “ሌላ ምን ምስክር ያስፈልገናል? 64.ስድቡን ሰምታችኋል፤ ታዲያ ምን ይመስላችኋል?”
እነርሱም ሞት ይገባዋል በማለት በአንድ ቃል ፈረዱበት። 65.በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ይተፉበት ጀመር፤ ዐይኑንም ሸፍነው በጡጫ እየመቱት፣ “ትንቢት ተናገር!” ይሉት ነበር። ጠባቂዎቹም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።
ጴጥሮስ ኢየሱስን አላውቀውም አለ
14፥66-72 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥69-75፤ ሉቃ 22፥56-62፤ ዮሐ 18፥16-18፤ 18፥25-27
66.ጴጥሮስ በግቢው ውስጥ በታችኛው በኩል ሳለ፣ ከሊቀ ካህናቱ የቤት ሠራተኞች አንዲቱ መጣች፤
67.ጴጥሮስ እሳት ሲሞቅ አይታ ትኵር ብላ ተመለከተችውና፣ “አንተም ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋራ ነበርህ” አለችው።
68.እርሱ ግን፣ “የምትዪውን እኔ ዐላውቀውም፤ አይገባኝምም” በማለት ካደ። ከዚያም ወደ መግቢያው በር ወጣ አለ፤ በዚህ ጊዜ ዶሮ ጮኸ።
69.ሠራተኛዪቱም ባየችው ጊዜ እዚያ ለቆሙት፣ “ይህ ሰው ከእነርሱ አንዱ ነው” ብላ እንደ ገና ተናገረች።
70.እርሱ ግን አሁንም ካደ።ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ በዚያ የቆሙት ሰዎች ጴጥሮስን፣ “የገሊላ ሰው እንደ መሆንህ መጠን፣ በርግጥ አንተ ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት። 71.እርሱ ግን፣ “እናንተ የምትሉትን ሰው እኔ አላውቀውም” እያለ ይምል ይገዘት ጀመር። 72.ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ። ጴጥሮስም፣ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው። ከዚያም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።