ሳምንት 6 · ቀን 29 (ሐሙስ)
📅 Tikimt 12, 2019
ኦሪት ዘጸአት 25, 26, 27 · መዝሙረ ዳዊት 90 · ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1
ኦሪት ዘጸአት
ምዕራፍ 25
ለመገናኛው ድንኳን የሚቀርቡ ስጦታዎች
25፥1-7 ተጓ ምብ – ዘፀ 35፥4-9
1.እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤
2.“ስጦታ እንዲያመጡልኝ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። ይሰጥ ዘንድ ልቡ ካነሣሣው ከእያንዳንዱ ሰው ስጦታን ተቀበልልኝ።
3.“ከእነርሱ የምትቀበላቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፤“ወርቅ፣ ብርና፣ ንሓስ፤ 4.ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጕር፤ 5.ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ፣ የለፋ ቈዳ፣ የግራር ዕንጨት፤ 6.ለመብራት የወይራ ዘይት፤
ለቅብዐ ዘይቱና ለጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፤ 7.በኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቍዎች። 8.“ከዚያም መቅደስ እንዲሠሩልኝ አድርግ፤ እኔም በመካከላቸው ዐድራለሁ። 9.ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ልክ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት።
የቃል ኪዳኑ ታቦት
25፥10-20 ተጓ ምብ – ዘፀ 37፥1-9
10.“ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት እንዲሠሩ አድርግ።
11.ውስጡንም ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አብጅለት።
12.አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ ሁለቱን በአንድ በኩል ሁለቱን በሌላ በኩል ከአራቱ እግሮች ጋራ አያይዝ።
13.ከዚያም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ በወርቅም ለብጣቸው።
14.መሎጊያዎችንም መሸከሚያ እንዲሆኑ በታቦቱ ማእዘኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው።
15.መሎጊያዎቹ ከታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ምን ጊዜም መውጣት የለባቸውም።
16.የምሰጥህንም ምስክር በታቦቱ ውስጥ አኑር።
17.“ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሥራለት።
18.በስርየት መክደኛው ዳርና ዳር ላይ የሚሆኑ ከወርቅ የተቀረጹ ሁለት ኪሩቤል ሥራ።
19.አንዱን ኪሩብ በአንደኛው፣ ሁለተኛውን ኪሩብ በሌላኛው ዳር አድርግ በሁለቱም ጫፎች ሁለቱን ኪሩቤል ከስርየት መክደኛው ጋራ አንድ ወጥ አድርገህ ሥራቸው።
20.ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይሸፍኑ፤ እርስ በርሳቸው ትይዩ በመሆንም ፊታቸውን ወደ ስርየት መክደኛው ያድርጉ።
21.የስርየት መክደኛውን በታቦቱ ዐናት ላይ አስቀምጠው፤ እኔ የምሰጥህን ምስክሩንም በታቦቱ ውስጥ አስቀምጥ።
22.በምስክሩ ታቦት ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከል፣ በስርየት መክደኛው ላይ በዚያ እኔ ከአንተ ጋራ እገናኛለሁ፤ ለእስራኤላውያን የሚሆኑትን ትእዛዞቼንም እሰጥሃለሁ።
የኅብስቱ ማስቀመጫ ጠረጴዛ
25፥23-29 ተጓ ምብ – ዘፀ 37፥10-16
23.“ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሥራ።
24.በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
25.ዙሪያውንም አንድ ስንዝር ስፋት ያለው ጠርዝ አብጅለት፤ በጠርዙም ዙሪያ የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
26.ለጠረጴዛው አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ፣ አራቱ እግሮች ባሉበት በአራቱ ማእዘኖች ላይ አያይዘው።
27.ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች ይይዙ ዘንድ፣ ቀለበቶቹ ከክፈፉ አጠገብ ይሁኑ።
28.መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሥራቸው፤ በወርቅ ለብጣቸው፤ ጠረጴዛውንም ተሸከምባቸው።
29.ለመጠጥ ቍርባን መፍሰሻ ይሆኑም ዘንድ ዝርግ ሳሕኖችንና ወጭቶችን፣ እንዲሁም ማንቈርቈሪያዎቹንና ጐድጓዳ ሳሕኖቹን ከንጹሕ ወርቅ ሥራቸው።
30.በማንኛውም ጊዜ በፊቴ እንዲሆን በገጸ ኅብስቱ በዚህ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጥ።
የመብራቱ መቅረዝ
25፥31-39 ተጓ ምብ – ዘፀ 37፥17-24
31.“ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ መቆሚያና ዘንግ አብጅለት፤ ጽዋ መሰል አበባዎች፣ እንቡጦችና የፈነዱ አበባዎች ከመቅረዙ ጋራ ወጥ ሆነው ይሠሩ።
32.ከመቅረዙ ግራና ቀኝ ጐን ጋራ የተያያዙ፣ በአንዱ በኩል ሦስት በሌላው በኩል ሦስት በድምሩ ስድስት ቅርንጫፎች ይኑሩት።
33.ከመቅረዙ ጋራ የተያያዙት ስድስቱ ቅርንጫፎች እያንዳንዳቸው እንቡጥና ቀንበጥ ያሏቸው የለውዝ አበባ ቅርጽ ያሏቸው ሦስት ጽዋ መሰል አበባዎች ጋራ ያኑሯቸው።
34.በመቅረዙም ላይ አበባዎች እንቡጥና ቀንበጥ ያሏቸው አራት የለውዝ አበባ ቅርጽ ያሏቸው ጽዋዎች ይኑሩ።
35.በመቅረዙ ላይ ላሉት ለስድስቱ ቅርንጫፎች እንቡጥ በመጀመሪያዎቹ ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር፣ ሁለተኛውም እንቡጥ በሁለተኛው ጥንድ ሥር፣ ሦስተኛውም እንቡጥ በሦስተኛው ጥንድ ሥር ይሁን።
36.እንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከመቅረዙ ጋራ አንድ ወጥ ሆነው ከንጹሕ ወርቅ ተቀርጸው ይሠሩ።
37.“ከዚያም ሰባት መብራቶች ሠርተህ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ለሚገኘው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጡ ከመቅረዙ ላይ አስቀምጣቸው።
38.መኰስተሪያና የኵስታሪ ማስቀመጫ ሳሕኖቹም ከንጹሕ ወርቅ ይሠሩ።
39.ለመቅረዙና ለዕቃዎቹ ሁሉ የሚያስፈልገው አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ነው።
40.በተራራው ላይ በተገለጠልህ ምሳሌ መሠረት መሥራትህን ልብ በል።
ምዕራፍ 26
የማደሪያው ድንኳን
26፥1-37 ተጓ ምብ – ዘፀ 36፥8-38
1.“በቀጭኑ ከተፈተለ የበፍታ ድርና በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ፤ እጀ ብልኅ ሠራተኛም ኪሩቤልን ይጥለፍባቸው።
2.መጋረጃዎች ሁሉ እኵል ይሁኑ፤ የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ ወርዱም አራት ክንድ ይሁን።
3.ዐምስቱን መጋረጃዎች አገጣጥመህ ስፋ፤ የቀሩትንም ዐምስት መጋረጃዎች እንደዚሁ አገጣጥመህ ስፋቸው።
4.ከዳር በኩል ባለው መጋረጃ ጠርዝ ላይ፣ ከሰማያዊ ጨርቅ የተሠሩ ቀለበቶች አድርግ፤ በሌላውም የመጋረጃ ጠርዝ ላይ እንዲሁ አድርግ።
5.ቀለበቶችን ትይዩ በማድረግ ዐምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው ጠርዝ መጋረጃ፣ ዐምሳ ቀለበቶችንም በሌላው ጠርዝ መጋረጃ አድርግ።
6.ከዚያም የመገናኛው ድንኳን አንድ ወጥ ይሆን ዘንድ መጋረጃዎቹን በአንድ ላይ ለማያያዝ ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሥራ።
7.“ማደሪያ ድንኳኑን ከላይ ሆነው የሚሸፍኑ በጠቅላላ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎች ሥራ።
8.ዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች እኩል ይሁኑ፤ የእያንዳንዱ ርዝመት ሠላሳ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ ይሁን።
9.ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ፣ እንደዚሁም ስድስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርገህ ስፋቸው፤ ከማደሪያው ድንኳን ፊት ለፊት ስድስተኛውን መጋረጃ ዕጠፍና በላዩ ላይ ደርበው።
10.በአንድ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ እንዲሁም በሌላ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን አድርግ።
11.ከዚያም ዐምሳ የንሓስ ማያያዣዎችን ሥራ፤ ድንኳኑን አንድ ወጥ አድርጎ ለማያያዝ በቀለበቶቹ ውስጥ ጨምራቸው።
12.ስለ ድንኳኑ መጋረጃዎች ትርፍ ቁመትም፣ ትርፍ ግማሽ መጋረጃ ከማደሪያው ድንኳን ጀርባ ላይ እንዲንጠለጠል ይሁን።
13.የድንኳኑ መጋረጃዎች በሁለቱም ጐኖች አንድ ክንድ ርዝመት ይኖራቸዋል፤ የተረፈውም የማደሪያውን ድንኳን ጐኖች እንዲሸፍን ሆኖ ይንጠለጠላል፤
14.ለድንኳኑ በቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ ልብስ አብጅ፤ በላዩም ላይ የአቆስጣ ቈዳ ይሁን።
15.“ለማደሪያው ድንኳን ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን አብጅ።
16.እያንዳንዱም ወጋግራ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን፤
17.ሁለት ጕጦችም ጐን ለጐን ይሁኑለት፤ የማደሪያውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚሁ መልክ አብጅ።
18.ለማደሪያው ድንኳን ክፍል በደቡብ በኩል ሃያ ወጋግራዎችን ሥራ።
19.ከሥራቸው የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ፤ በእያንዳንዱ ጕጠት ሥር አንድ መቆሚያ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ።
20.በሌላው ጐን፣ ከማደሪያው ድንኳን በስተሰሜን በኩል ሃያ ወጋግራዎችን አብጅ፤
21.በእያንዳንዱም ወጋግራ ሥር ሁለት ሁለት መቆሚያ ሆኖ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ።
22.በዳር በኩል ለሚገኘው ይኸውም በምዕራብ ጠርዝ ላለው የማደሪያው ድንኳን ስድስት ወጋግራዎች አብጅ።
23.ዳርና ዳር ላሉት ማእዘኖች ሁለት ወጋግራዎች አብጅ።
24.በእነዚህ ሁለት ማእዘኖች ላይ ከታች እስከ ላይ ድረስ ድርብ ሲሆኑ፣ በአንድ ቀለበት ውስጥ የሚገጥሙ መሆን አለባቸው፤ በሁለቱም ወገን እንዲሁ መሆን አለበት።
25.ስለዚህ ስምንት ወጋግራዎች አሉ፤ እንዲሁም ዐሥራ ስድስት የብር መቆሚያዎች ሲኖሩ፣ ለእያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ሁለት መቆሚያ ይሆናል።
26.“ደግሞም ከግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን አብጅ፤ በአንድ በኩል ላሉት የማደሪያው ድንኳን ወጋግራዎች ዐምስት፣
27.በሌላው ጐን ላሉት ዐምስት፣ በማደሪያው ድንኳን ዳር በምዕራብ በኩል ባሉት ወጋግራዎች ዐምስት አብጅ።
28.መካከለኛው አግዳሚ በወጋግራዎቹ መካከል ከጫፍ እስከ ጫፍ ይተላለፍ።
29.ወጋግራዎቹን በወርቅ ለብጣቸው፤ አግዳሚዎቹን ለመያዝ የወርቅ ቀለበቶች አብጅ፤ አግዳሚዎቹንም በወርቅ ለብጣቸው።
30.“ማደሪያ ድንኳኑንም በተራራው ላይ ባየኸው ዕቅድ መሠረት ትከለው።
31.“ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ መጋረጃ ሥራ፤ እጀ ጥበብ ባለሙያም ኪሩቤልን ይጥለፍበት።
32.በወርቅ በተለበጡ ከግራር ዕንጨት በተሠሩና በአራቱ የብር መቆሚያዎች ላይ በቆሙት በአራቱ ምሰሶዎች፣ በወርቅ ኵላቦች ላይ አንጠልጥለው።
33.መጋረጃውን በማያያዣዎቹ ላይ ስቀለው፤ የምስክሩንም ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ አስቀምጠው፤ መጋረጃውም መቅደሱን ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል።
34.በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ የማስተስረያውን ክዳን አስቀምጥ።
35.ጠረጴዛውን ከመገናኛው ድንኳን በሰሜን በኩል ከመጋረጃው ውስጥ አስቀምጠው፤ መቅረዙንም ከርሱ ትይዩ በማድረግ በደቡብ በኩል አድርገው።
36.“ለድንኳኑ ደጃፍ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ በጥልፍ ዐዋቂ የተጠለፈ መጋረጃ አብጅ።
37.ለዚህም መጋረጃ የወርቅ ኵላቦችንና ከግራር ዕንጨት የተሠሩ፣ በወርቅ የተለበጡ ዐምስት ምሰሶዎችን አብጅ፤ ዐምስት የንሓስ መቆሚያዎችንም አብጅላቸው።
ምዕራፍ 27
የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረቢያ መሠዊያ
27፥1-8 ተጓ ምብ – ዘፀ 38፥1-7
1.“ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ ርዝመቱ ዐምስት፣ ወርዱም ዐምስት ክንድ ሆኖ ባለአራት ማእዘን ይሁን።
2.ቀንዶቹና መሠዊያው አንድ ወጥ ይሆኑ ዘንድ በአራቱም ማእዘኖች ላይ ቀንድ አድርግለት፤ መሠዊያውንም በንሓስ ለብጠው።
3.ዕቃዎቹን ሁሉ ይኸውም የዐመድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ከንሓስ አብጃቸው።
4.ዐመድ ማውረጃ የሚሆን እንደ መረብ የሆነ የንሓስ ፍርግርግ አድርግለት በአራቱም የመረብ ማእዘኖች ላይ የንሓስ ቀለበቶች አብጅ።
5.እስከ መሠዊያው ወገብ እንዲደርስ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን ሥር አድርገው።
6.የግራር ዕንጨት መሎጊያዎችን ለመሠዊያው ሠርተህ በንሓስ ለብጣቸው።
7.በሸክም ጊዜ በመሠዊያው ሁለቱም ጐኖች እንዲሆኑ፣ መሎጊያዎቹ በቀለበቶቹ ውስጥ ይግቡ።
8.መሠዊያውን ውስጡን ባዶ ከሆኑ ሳንቃዎች አብጀው፤ ልክ በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ይበጅ።
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ
27፥9-19 ተጓ ምብ – ዘፀ 38፥9-20
9.“ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ አብጅለት፤ በደቡብ በኩል ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ይሁን፤ ከቀጭን በፍታ የተፈተሉ መጋረጃዎች፣
10.ሃያ ምሰሶዎች፣ ሃያ የንሓስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ይኑሩት።
11.በሰሜኑም በኩል አንድ መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይሁኑ፤ ሃያ ምሰሶዎቹ፣ ሃያ የንሓስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎችም ላይ ዘንጎች ይኑሩ።
12.“የአደባባዩ ምዕራብ ጫፍ ስፋቱ ዐምሳ ክንድ ሆኖ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎች ያሉት መጋረጃዎች ይኑሩት።
13.በምሥራቅ ጫፍ በፀሓይ መውጫ በኩል ያለው አደባባይ አሁንም ዐምስት ክንድ ስፋት ይኑረው።
14.ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በአንድ በኩል ባለው ደጃፍ ይሁኑ።
15.ሦስት ምሰሶዎች ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በሌላው በኩል ይሁኑ።
16.“ለአደባባዩ መግቢያ አራት ምሰሶዎችና አራት መቆሚያዎች ያሉት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከቀጭን በፍታ የተፈተለ፣ ጥልፍ ጠላፊ የጠለፈበት ሃያ ክንድ ርዝመት ያለው መጋረጃ ይሁን።
17.በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ ኵላቦችና የንሓስ መቆሚያዎች ይኑሯቸው።
18.አደባባዩ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱ ዐምሳ ክንድ ሆኖ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ማግ ቁመታቸው ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎችና የንሓስም መቆሚያዎች ያሉት ይሁን።
19.ጥቅማቸው ምንም ዐይነት ይሁን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ከንሓስ የተሠሩ ይሁኑ።
የመቅረዙ ዘይት
27፥20-21 ተጓ ምብ – ዘሌ 24፥1-3
20.“መብራቶቹ ያለማቋረጥ እንዲያበሩ ለመብራቱ የሚሆን ከወይራ ተጨምቆ የተጠለለ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን እዘዛቸው።
21.በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተውጭ ይኸውም ከምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት፣ አሮንና ወንድ ልጆቹ መብራቶቹን ከምሽት እስከ ንጋት በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።
መዝሙረ ዳዊት
ምዕራፍ 90
1.አራተኛ መጽሐፍ
ከመዝሙር 90–106
የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት።
1 ጌታ ሆይ፤
አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን። 2.ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣
ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣
አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ። 3.ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤
“የሰው ልጆች ሆይ፤ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ” ትላለህ፤ 4.ሺሕ ዓመት በፊትህ፣
እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣
እንደ ሌሊትም እርቦ ነውና። 5.እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበንናሉ፤
እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤ 6.ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤
ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል። 7.በቍጣህ አልቀናልና፤
በመዓትህም ደንግጠናል። 8.በደላችንን በፊትህ፣
የተሰወረ ኀጢአታችንንም በገጽህ ብርሃን ፊት አኖርህ። 9.ዘመናችን ሁሉ በቍጣህ ዐልፏልና፤
ዕድሜያችንንም በመቃተት እንጨርሳለን። 10.የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤
ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤
ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን። 11.የቍጣህን ኀይል ማን ያውቃል?
መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው። 12.ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣
ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን። 13.እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል?
ለአገልጋዮችህም ራራላቸው። 14.በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣
ሐሤትም እንድናደርግ፣
ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን። 15.መከራ ባሳየኸን ዘመን መጠን፣
ክፉም ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሠኘን። 16.ሥራህ ለአገልጋዮችህ፣
ክብርህም ለልጆቻቸው ይገለጥ። 17.የጌታ የአምላካችን ሞገስ በላያችን ይሁን፤
የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን፤
አዎን፣ ፍሬያማ አድርግልን።
ከመዝሙር 90–106
የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት።
1 ጌታ ሆይ፤
አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን። 2.ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣
ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣
አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ። 3.ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤
“የሰው ልጆች ሆይ፤ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ” ትላለህ፤ 4.ሺሕ ዓመት በፊትህ፣
እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣
እንደ ሌሊትም እርቦ ነውና። 5.እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበንናሉ፤
እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤ 6.ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤
ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል። 7.በቍጣህ አልቀናልና፤
በመዓትህም ደንግጠናል። 8.በደላችንን በፊትህ፣
የተሰወረ ኀጢአታችንንም በገጽህ ብርሃን ፊት አኖርህ። 9.ዘመናችን ሁሉ በቍጣህ ዐልፏልና፤
ዕድሜያችንንም በመቃተት እንጨርሳለን። 10.የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤
ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤
ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን። 11.የቍጣህን ኀይል ማን ያውቃል?
መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው። 12.ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣
ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን። 13.እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል?
ለአገልጋዮችህም ራራላቸው። 14.በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣
ሐሤትም እንድናደርግ፣
ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን። 15.መከራ ባሳየኸን ዘመን መጠን፣
ክፉም ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሠኘን። 16.ሥራህ ለአገልጋዮችህ፣
ክብርህም ለልጆቻቸው ይገለጥ። 17.የጌታ የአምላካችን ሞገስ በላያችን ይሁን፤
የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን፤
አዎን፣ ፍሬያማ አድርግልን።
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
ምዕራፍ 1
1.በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤
በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉ፣ ለታመኑ፣ በኤፌሶን ለሚገኙ ቅዱሳን፤ 2.ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉ፣ ለታመኑ፣ በኤፌሶን ለሚገኙ ቅዱሳን፤ 2.ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።