ሳምንት 4 · ቀን 20 (አርብ)
📅 Meskerem 29, 2019
ኦሪት ዘፍጥረት 49, 50 · ወደ ገላትያ ሰዎች 4
ኦሪት ዘፍጥረት
ምዕራፍ 49
ያዕቆብ ልጆቹን ባረከ
49፥1-28 ተጓ ምብ – ዘዳ 33፥1-29
1.ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በኋለኛው ዘመን ምን እንደሚደርስባችሁ እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ፤
2.“እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ተሰብሰቡና ስሙ፤
አባታችሁ እስራኤልንም ስሙ። 3.“ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤
ኀይሌና የጕብዝናዬም መጀመሪያ፤
በክብር ትልቃለህ፤ በኀይልም
ትበልጣለህ። 4.እንደ ውሃ የዋለልህ ነህና እልቅና
አይኖርህም፤
የአባትህን መኝታ ደፍረሃል፤
ምንጣፌንም አርክሰሃል። 5.“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣
ሰይፎቻቸው የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው። 6.ወደ ሸንጓቸው አልግባ፤
ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፤
በቍጣ ተነሣሥተው ሰዎችን ገድለዋል፤
የበሬዎችንም ቋንጃ እንዳሻቸው ቈራርጠዋል። 7.እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣
ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤
በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤
በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ። 8.“ይሁዳ፣ ወንድሞችህ ይወድሱሃል፤
እጅህም የጠላቶችህን ዐንገት ዐንቆ ይይዛል፤
የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይሰግዱልሃል። 9.አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤
ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣
እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤
እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤
ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል? 10.በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤
የገዢነት ምርኵዝም ከእግሮቹ መካከል።
ገዥነት የሚገባው እስኪመጣ ድረስ፣
ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙታል። 11.አህያውን በወይን ግንድ፣
ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ
ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤
ልብሱን በወይን ጠጅ፣
መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል። 12.ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣
ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ። 13.“ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤
የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤
ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል። 14.“ይሳኮር፣ በበጎች ጕረኖም መካከል የሚተኛ
ዐጥንተ ብርቱ አህያ ነው። 15.ማረፊያ ቦታው መልካም፣
ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣
ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል፤
ተገድዶም ያገለግላል። 16.“ዳን፣ ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ፣
በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል። 17.ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣
የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤
ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣
የፈረሱን ሰኰና ይነክሳል። 18.“እግዚአብሔር ሆይ፤ ማዳንህን እጠባበቃለሁ። 19.“ጋድን ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፤
እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል። 20.“አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤
ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል። 21.“ንፍታሌም ነጻ እንደ ተለቀቀች፣
የሚያማምሩም ግልገሎች
እንደምትወልድ ሚዳቋ ነው።
22.“ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው።
ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ። 23.ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት፤
በጥላቻም ነደፉት። 24.ነገር ግን በያዕቆብ ኀያል አምላክ ክንድ፣
እረኛው በሆነው በእስራኤል ዐለት፣ ቀስቱ ጸና፤
ጠንካራ ክንዱም ቀለጠፈ። 25.አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣
በሚባርክህ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ፣
ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣
ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣
ከማሕፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል። 26.ከጥንት ተራሮች በረከት፣
ከዘላለም ኰረብቶች ምርቃት ይልቅ፣
የአባትህ በረከት ይበልጣል።
ይህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤
በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ። 27.“ብንያም፣ ነጣቂ ተኵላ ነው፤
ያደነውን ማለዳ ይበላል፤
የማረከውን ማታ ይከፋፈላል።” 28.እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።
የያዕቆብ መሞት
29.ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እነሆ፤ ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሷል፤ በኬጢያዊው በኤፍሮን ዕርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤ 30.ይህ በከነዓን ምድር፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ ውስጥ ያለው ዋሻ፣ የመቃብር ቦታ እንዲሆን አብርሃም ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ ከነዕርሻ ቦታው የገዛው ነው። 31.በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይሥሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤ 32.እኔም ልያን የቀበርኋት እዚያው ነው። መስኩና ዋሻው የተገዙት ከኬጢያውያን ላይ ነው።” 33.ያዕቆብ እነዚህን ቃላት ለልጆቹ ተናግሮ እንዳበቃ፣ እግሮቹን በዐልጋው ላይ ሰብስቦ፣ የመጨረሻ ትንፋሹን ተነፈሰ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።ምዕራፍ 50
1.ዮሴፍ በአባቱ ፊት ተደፍቶ አለቀሰ፤ ሳመውም።
2.ከዚያም ዮሴፍ የአባቱ የእስራኤል ሬሳ እንዳይፈርስ ባለመድኀኒት የሆኑ አገልጋዮቹ በመድኀኒት እንዲቀቡት አዘዘ። ባለመድኀኒቶቹም እንዳይፈርስ ሬሳውን በመድኀኒት ቀቡት።
3.ሬሳው እንዳይፈርስ መድኀኒት መቀባቱ በአገሩ ልማድ መሠረት አርባ ቀን ወሰደባቸው፤ ግብጻውያንም ሰባ ቀን አለቀሱለት።
4.የሐዘኑ ጊዜ እንዳበቃ ዮሴፍ የፈርዖንን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “በፊታችሁ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩልኝ፤
5.‘የምሞትበት ጊዜ ስለ ተቃረበ፣ በከነዓን ምድር ራሴ ቈፍሬ በአዘጋጀሁት መቃብር እንድትቀብረኝ’ ሲል አባቴ አስምሎኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ልቅበር፤ ከዚያም እመለሳለሁ።”
6.ፈርዖንም፣ “በአስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው።
7.ከዚያም ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ወጣ፤ የፈርዖን ሹማምት በሙሉ፣ የቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንዲሁም የግብጽ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ሁሉ ተከተሉት።
8.እንደዚሁም የዮሴፍ ቤተ ሰዎች፣ ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተ ሰዎች በሙሉ ዐብረውት ሄዱ። በጌሤም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፣ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋዎቻቸው ብቻ ነበሩ።
9.እንዲሁም ሠረገሎችና ፈረሰኞች ዐብረውት ወጡ፤ አጀቡም እጅግ ብዙ ነበረ።
10.እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።
11.በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ ዐውድማ የተደረገውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ለግብጻውያን መራራ ልቅሷቸው ነው” አሉ። በዮርዳኖስ አጠገብ ያለው የዚያ ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ተብሎ መጠራቱም ከዚሁ የተነሣ ነበር።
12.የያዕቆብ ልጆችም አባታቸው እንዳዘዛቸው አደረጉ፤
13.አስከሬኑን ወደ ከነዓን ምድር ወስደው አብርሃም ከኬጢያዊው ከኤፍሮን ላይ ከነዕርሻው በገዛው፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ በሚገኘው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።
14.ዮሴፍ አባቱን ከቀበረ በኋላ፣ ከወንድሞቹና ለአባቱ ቀብር ዐብረውት ሄደው ከነበሩት ሁሉ ጋራ ወደ ግብጽ ተመለሰ።
ዮሴፍ ወንድሞቹን እንደማይበቀላቸው አረጋገጠ
15.የዮሴፍ ወንድሞች ከአባታቸው ሞት በኋላ፣ “ከፈጸምንበት በደል የተነሣ ዮሴፍ ቂም ይዞ ቢበቀለን ምን እናደርጋለን?” ተባባሉ። 16.ስለዚህ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ዮሴፍ ላኩ፤ “አባትህ ከመሞቱ በፊት እንዲህ የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር፤ 17.‘ለዮሴፍ፣ “ወንድሞችህ በአንተ ላይ የፈጸሙትን ኀጢአትና ክፉ በደል ይቅር በላቸው” ብላችሁ ንገሩት።’ አሁንም የእኛን የአባትህን አምላክ አገልጋዮች ኀጢአት ይቅር በለን።” መልእክታቸው ሲደርሰው ዮሴፍ አለቀሰ። 18.ከዚያም ወንድሞቹ መጡና በፊቱ ተደፍተው፣ “እኛ የአንተ ባሮች ነን” አሉት። 19.ዮሴፍ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ እኔን በእግዚአብሔር ቦታ ማን አስቀመጠኝ? 20.እናንተ እኔን ለመጕዳት ዐስባችሁ አድርጋችሁት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደሚታየው ሁሉ የብዙዎችን ሕይወት ለማዳን ለበጎ ነገር አዋለው። 21.አሁንም ቢሆን አትፍሩ፤ ለእናንተና ለልጆቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” በማለት አረጋግጦ፣ በደግ ቃል አናገራቸው።የዮሴፍ መሞት
22.ዮሴፍ ከአባቱ ቤተ ሰቦች ጋራ በግብጽ ተቀመጠ፤ አንድ መቶ ዐሥር ዓመትም ኖረ፤ 23.የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ አየ። የምናሴ ልጅ ማኪር የወለዳቸውም ልጆች በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ። 24.ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን፣ “እነሆ፤ የመሞቻዬ ጊዜ ተቃርቧል፤ እግዚአብሔርም በረድኤቱ ይጐበኛችሁና ከዚህ አገር ያወጣችኋል፤ ለአባቶቻችን ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባችኋል” አላቸው። 25.ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፣ “እግዚአብሔር በረድኤቱ ያስባችኋል፤ በዚያ ጊዜ ዐፅሜን ከዚህ አገር ይዛችሁ እንድትወጡ” ሲል አስማላቸው። 26.ዮሴፍም በመቶ ዐሥር ዓመቱ ሞተ፤ ሬሳው እንዳይፈርስ በአገሩ ደንብ በመድኀኒት ከደረቀ በኋላ፣ ሣጥን ውስጥ አስገብተው በግብጽ ምድር አስቀመጡት።ወደ ገላትያ ሰዎች
ምዕራፍ 4
1.እኔ የምለው ይህ ነው፤ ወራሹ ሕፃን እስከ ሆነ ድረስ፣ ሀብት ሁሉ የርሱ ቢሆንም እንኳ፣ ከባሪያ የተለየ አይደለም።
2.አባቱ እስከ ወሰነለት ጊዜ ድረስ በጠባቂዎችና በሞግዚቶች ሥር ነው።
3.እኛም እንዲሁ ገና ልጆች በነበርንበት ጊዜ፣ ከዓለም መሠረታዊ መንፈሳዊ ኀይሎች ሥር በመሆን በባርነት ተገዝተን ነበር።
4.ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
5.ይህም የሆነው የልጅነትን መብት እናገኝ ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት ነው።
6.ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር፣ “አባ፣ አባት” ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ።
7.ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ስለ ሆንህ፣ እግዚአብሔር ወራሽ አድርጎሃል።
“አንቺ የማትወልጅ መካን ሆይ፤
ደስ ይበልሽ፤
አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣
በእልልታ ጩኺ፤
ባል ካላት ይልቅ፣
የብቸኛዪቱ ልጆች በዝተዋልና።” 28.እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ እናንተም እንደ ይሥሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ናችሁ። 29.በዚያ ጊዜ እንደ ሥጋ ልማድ የተወለደው ልጅ፣ በመንፈስ ኀይል የተወለደውን አሳደደው፤ አሁንም እንደዚያው ነው። 30.ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? “ባሪያዪቱን ከነልጇ አባርራት፤ የባሪያዪቱ ልጅ ከነጻዪቱ ልጅ ጋራ አይወርስምና።” 31.ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ የነጻዪቱ እንጂ የባሪያዪቱ ልጆች አይደለንም።
ጳውሎስ ስለ ገላትያ ሰዎች ማሰቡ
8.እግዚአብሔርን ከማወቃችሁ በፊት፣ በባሕርያቸው አማልክት ላልሆኑት ባሪያዎች ነበራችሁ፤ 9.አሁን ግን እግዚአብሔርን ዐውቃችሁታል፤ ይልቁን ደግሞ በእግዚአብሔር ታውቃችኋል። ታዲያ እንደ ገና ወደ ደካማና ወደማይጠቅም ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? ዳግም በርሱ በባርነት ለመጠመድ ትፈልጋላችሁን? 10.ልዩ የሆኑ ቀኖችን፣ ወሮችን፣ ወቅቶችንና ዓመታትን ታከብራላችሁ! 11.ስለ እናንተ በከንቱ የደከምሁ እየመሰለኝ እፈራላችኋለሁ። 12.ወንድሞች ሆይ፤ እለምናችኋለሁ፤ እኔ እናንተን እንደ መሰልሁ፣ እናንተም እኔን ምሰሉ። እናንተ አንዳች አልበደላችሁኝም። 13.እንደምታውቁት፣ በመጀመሪያ ለእናንተ ወንጌልን የሰበክሁት በሕመም ምክንያት ነበር። 14.ሕመሜ ለእናንተ ፈተና ሆኖባችሁም እንኳ፣ አልሰለቻችሁኝም፤ ወይም አልተጸየፋችሁኝም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ፣ እንዲያውም እንደ ራሱ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ አድርጋችሁ ተቀበላችሁኝ። 15.ለመሆኑ ያ ሁሉ ደስታችሁ የት ደረሰ? ቢቻላችሁ ዐይናችሁን ቢሆን እንኳ አውጥታችሁ የምትሰጡኝ እንደ ነበራችሁ እመሰክራለሁ። 16.እውነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላት ሆንሁባችሁን? 17.እነዚያ ሰዎች ወደ ራሳቸው ሊወስዷችሁ ይተጋሉ፤ ለበጎ ግን አይደለም፤ የሚፈልጉት እናንተን ከእኛ ነጥለው የራሳቸው ሊያደርጓችሁ ነው። 18.ለበጎ እስከ ሆነ ድረስ ተቈርቋሪ መሆን መልካም ነው፤ ይህም መሆን የሚገባው ዘወትር እንጂ እኔ ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ብቻ አይደለም። 19.የምወድዳችሁ ልጆቼ ሆይ፤ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ፣ ስለ እናንተ እንደ ገና ምጥ ይዞኛል፤ 20.ስለ እናንተ ግራ በመጋባት ተጨንቄአለሁና፤ አሁን በመካከላችሁ ተገኝቼ ለየት ባለ ቋንቋ ልናገራችሁ ምን ያህል በወደድሁ!አጋርና ሣራ
21.እናንተ ከኦሪት ሕግ በታች ለመኖር የምትሹ እስኪ ንገሩኝ፤ ሕግ ምን እንደሚል አልሰማችሁምን? 22.አብርሃም፣ አንዱ ከባሪያዪቱ፣ ሌላው ደግሞ ከነጻዪቱ ሴት የሆኑ ሁለት ልጆች እንደ ነበሩት ተጽፏልና። 23.ባሪያ ከነበረችው ሴት የተገኘው ልጅ እንደ ሥጋ ልማድ ነበር፤ ከነጻዪቱ ሴት የተወለደው ግን በተስፋው ቃል መሠረት ነበር። 24.እነዚህ ሴቶች ሁለቱን ኪዳኖች ስለሚያመለክቱ፣ ይህ ሁኔታ እንደ ምሳሌ የሚታይ ነው። አንደኛዋ ኪዳን ከሲና ተራራ ስትሆን፣ ለባርነት የሚሆኑ ልጆችን የምትወልድ ናት፤ እርሷም አጋር ናት። 25.እንግዲህ አጋር በዐረብ አገር ያለችው የሲናን ተራራ በመወከል አሁን ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፤ ከልጇ ጋራ በባርነት ናትና። 26.ከላይ የሆነችው ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት ትኖራለች፤ እርሷም እናታችን ናት። 27.እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦“አንቺ የማትወልጅ መካን ሆይ፤
ደስ ይበልሽ፤
አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣
በእልልታ ጩኺ፤
ባል ካላት ይልቅ፣
የብቸኛዪቱ ልጆች በዝተዋልና።” 28.እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ እናንተም እንደ ይሥሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ናችሁ። 29.በዚያ ጊዜ እንደ ሥጋ ልማድ የተወለደው ልጅ፣ በመንፈስ ኀይል የተወለደውን አሳደደው፤ አሁንም እንደዚያው ነው። 30.ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? “ባሪያዪቱን ከነልጇ አባርራት፤ የባሪያዪቱ ልጅ ከነጻዪቱ ልጅ ጋራ አይወርስምና።” 31.ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ የነጻዪቱ እንጂ የባሪያዪቱ ልጆች አይደለንም።