ሳምንት 1 · ቀን 1 (ሰኞ)
📅 Meskerem 4, 2019
ኦሪት ዘፍጥረት 1, 2 · መዝሙረ ዳዊት 19 · የማርቆስ ወንጌል 1
ኦሪት ዘፍጥረት
ምዕራፍ 1
የፍጥረት አጀማመር
1.በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። 2.ምድርም ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች። የምድርን ጥልቅ ስፍራ ሁሉ ጨለማ ውጦት ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር። 3.እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። 4.እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ ብርሃኑን ከጨለማ ለየ። 5.እግዚአብሔርም ብርሃኑን “ቀን”፣ ጨለማውን “ሌሊት” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ የመጀመሪያ ቀን። 6.እግዚአብሔር፣ “ውሃን ከውሃ የሚለይ ጠፈር በውሆች መካከል ይሁን” አለ። 7.ስለዚህ እግዚአብሔር ጠፈርን አድርጎ ከጠፈሩ በላይና ከጠፈሩ በታች ያለውን ውሃ ለየ፤ እንዳለውም ሆነ። 8.እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን። 9.ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ ደረቁ ምድር ይገለጥ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። 10.እግዚአብሔር ደረቁን ምድር፣ “የብስ”፣ በአንድነት የተሰበሰበውን ውሃ፣ “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። 11.እግዚአብሔር፣ “ምድር ዕፀዋትንም፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በምድር ላይ ዘር ያዘሉ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። 12.ምድር ዕፀዋትን፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በውስጣቸው ዘር ያለባቸው ፍሬ የሚያፈሩትን ዛፎች በየወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። 13.መሸ፤ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን። 14.ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ቀኑን ከሌሊት እንዲለዩ፣ የዓመት ወቅቶች፣ ቀናትና ዓመታት የሚጀምሩበትንም እንዲያመለክቱ፣ 15.ለምድር ብርሃን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ይሁኑ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። 16.እግዚአብሔር፣ ለምድር ብርሃን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናት አደረገ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሠለጥን አደረገ። እንዲሁም ከዋክብትን አደረገ። 17.ለምድር ብርሃን እንዲሰጡ እግዚአብሔር እነዚህን በሰማይ ጠፈር አኖራቸው። 18.ይኸውም በቀንና በሌሊት እንዲሠለጥኑ፣ ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። 19.መሸ፤ ነጋም፣ አራተኛ ቀን። 20.እግዚአብሔር፣ “ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። 21.በዚህ መሠረት፣ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ታላላቅ ፍጥረታትን፣ በውሃ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እንደየወገናቸው እንዲሁም ክንፍ ያላቸውን ወፎች ሁሉ እንደየወገናቸው ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። 22.እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕርንም ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። 23.መሸ፤ ነጋም፤ ዐምስተኛ ቀን። 24.እግዚአብሔር፣ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። 25.እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። 26.እግዚአብሔር፣ “ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንሥራ፤ በባሕር ዓሦች፣ በሰማይ ወፎች፣ በከብቶች፣ በምድር ሁሉ ላይ፣ እንዲሁም በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ። 27.ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤
ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። 28.እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ግዟቸው” ብሎ ባረካቸው። 29.እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “በምድር ላይ ያሉትን ዘር የሚሰጡ ተክሎችን ሁሉ፣ በፍሬአቸው ውስጥ ዘር ያለባቸውን ዛፎች ሁሉ ምግብ ይሆኑላችሁ ዘንድ ሰጥቻችኋለሁ። 30.እንዲሁም ለምድር አራዊት ሁሉ፣ ለሰማይ ወፎች ሁሉ፣ በምድር ላይ ለሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ” እንዳለውም ሆነ። 31.እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፣ እጅግ መልካም ነበረ። መሸ፤ ነጋም፤ ስድስተኛ ቀን።
ምዕራፍ 2
1.የሰማያትና የምድር፣ በውስጣቸውም ያሉት ሁሉ አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ።
2.እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራውን በሰባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ይሠራ ከነበረው ሥራው ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።
3.እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም፤ ካከናወነው የመፍጠር ሥራው ሁሉ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነውና።
ይሁን እንጂ ለአዳም ተስማሚ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። 21.እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐድኑ አንዲት ዐጥንት ወስዶ፣ ስፍራውን በሥጋ ሞላው። 22.እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም የወሰዳትን ዐጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። 23.አዳምም እንዲህ አለ፤
“እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣
ሥጋም ከሥጋዬ ናት።
ከወንድ ተገኝታለችና ‘ሴት’ ትባል።” 24.ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። 25.አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም ዕራቍታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።
አዳምና ሔዋን
4.እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ የተከናወኑት እንደዚህ ነበረ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን ሲፈጥር፣ 5.የሜዳ ቡቃያ ገና በምድር ላይ አልታየም፤ የሜዳ ተክልም ገና አልበቀለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክ በመሬት ላይ ገና ዝናብ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚያለማ ሰው አልነበረም። 6.ነገር ግን ውሃ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር። 7.እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ። 8.እግዚአብሔር አምላክ በምሥራቅ፣ በዔድን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፤ ያበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው። 9.እግዚአብሔር አምላክም ለዐይን የሚያስደስት ለመብልም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በአትክልቱ ቦታ መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም መልካምና ክፉን መለየት የሚያስችለው የዕውቀት ዛፍ ነበረ። 10.የአትክልት ስፍራውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔድን ይፈስስ ነበር፤ ከዚያም በአራት ተከፍሎ ይወጣ ነበር። 11.የመጀመሪያው፣ ወርቅ በሚገኝበት በኤውላጥ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የፊሶን ወንዝ ነው። 12.ኤውላጥ ምርጥ የሆነ ወርቅ፣ መልካም መዐዛ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኙበት ምድር ነው። 13.ሁለተኛው፣ በኢትዮጵያ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የግዮን ወንዝ ነው። 14.ሦስተኛው፣ ከአሦር በስተምሥራቅ የሚፈስሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን፣ አራተኛው የኤፍራጥስ ወንዝ ነው። 15.እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወስዶ እንዲያለማትና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በዔድን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው። 16.እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ በማለት አዘዘው፤ “በአትክልት ስፍራው ውስጥ ከሚገኝ ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ ትበላለህ። 17.ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ምክንያቱም ከርሱ በበላህ ቀን በርግጥ ትሞታለህ።” 18.ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፣ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ” አለ። 19.እግዚአብሔር አምላክ የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጥረታት ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ። 20.ስለዚህ አዳም ለከብቶች፣ ለሰማይ ወፎች፣ ለዱር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው።ይሁን እንጂ ለአዳም ተስማሚ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። 21.እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐድኑ አንዲት ዐጥንት ወስዶ፣ ስፍራውን በሥጋ ሞላው። 22.እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም የወሰዳትን ዐጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። 23.አዳምም እንዲህ አለ፤
“እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣
ሥጋም ከሥጋዬ ናት።
ከወንድ ተገኝታለችና ‘ሴት’ ትባል።” 24.ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። 25.አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም ዕራቍታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።
መዝሙረ ዳዊት
ምዕራፍ 19
1.ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።
1 ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤
የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ። 2.ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤
ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤ 3.ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤
ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም። 4.ያም ሆኖ ድምፃቸው በምድር ሁሉ፣
ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣል።
እርሱ በሰማያት ለፀሓይ ድንኳን ተክሏል፤ 5.ፀሓይም ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ ይወጣል፤
ወደ ግቡም እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል። 6.መውጫው ከሰማያት ዳርቻ ነው፤
ዑደቱም እስከ ሌላው ዳርቻ ነው፤
ከትኵሳቱም የሚሰወር የለም። 7.የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤
ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤
የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤
አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል። 8.የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤
ልብን ደስ ያሰኛሉ።
የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤
ዐይንን ያበራል። 9.እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤
ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣
ሁለንተናውም ጻድቅ ነው። 10.ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣
እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤
ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤
ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል። 11.ደግሞም አገልጋይህ በርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል፤
እርሱንም መጠበቅ ወሮታ አለው። 12.ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል?
ከተሰወረ በደል አንጻኝ። 13.ባሪያህን ከድፍረት ኀጢአት ጠብቅ፤
እንዳይሠለጥንብኝም ርዳኝ፤
ያን ጊዜ ያለ እንከን እሆናለሁ፤
ከታላቅ በደልም እነጻለሁ። 14.ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤
የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣
በፊትህ ያማረ ይሁን።
1 ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤
የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ። 2.ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤
ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤ 3.ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤
ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም። 4.ያም ሆኖ ድምፃቸው በምድር ሁሉ፣
ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣል።
እርሱ በሰማያት ለፀሓይ ድንኳን ተክሏል፤ 5.ፀሓይም ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ ይወጣል፤
ወደ ግቡም እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል። 6.መውጫው ከሰማያት ዳርቻ ነው፤
ዑደቱም እስከ ሌላው ዳርቻ ነው፤
ከትኵሳቱም የሚሰወር የለም። 7.የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤
ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤
የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤
አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል። 8.የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤
ልብን ደስ ያሰኛሉ።
የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤
ዐይንን ያበራል። 9.እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤
ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣
ሁለንተናውም ጻድቅ ነው። 10.ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣
እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤
ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤
ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል። 11.ደግሞም አገልጋይህ በርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል፤
እርሱንም መጠበቅ ወሮታ አለው። 12.ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል?
ከተሰወረ በደል አንጻኝ። 13.ባሪያህን ከድፍረት ኀጢአት ጠብቅ፤
እንዳይሠለጥንብኝም ርዳኝ፤
ያን ጊዜ ያለ እንከን እሆናለሁ፤
ከታላቅ በደልም እነጻለሁ። 14.ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤
የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣
በፊትህ ያማረ ይሁን።
የማርቆስ ወንጌል
ምዕራፍ 1
የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት
1፥2-8 ተጓ ምብ – ማቴ 3፥1-11፤ ሉቃ 3፥2-16
1.የእግዚአብሔር ልጅ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።
2.በነቢዩ በኢሳይያስ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤“እነሆ፤ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን
በፊትህ እልካለሁ፤” 3.“የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤
‘ጥርጊያውንም አስተካክሉ’
እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ድምፅ።” 4.ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሓ እያጠመቀና ለኀጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ። 5.በመላው ይሁዳ፣ የኢየሩሳሌም ሰዎችም በጠቅላላ ወደ እርሱ በመሄድ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በርሱ እጅ ተጠመቁ። 6.ዮሐንስ የግመል ጠጕር ይለብስ፣ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ፣ አንበጣና የበረሓ ማርም ይበላ ነበር። 7.ስብከቱም፣ “እኔ ጐንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ፣ ከእኔ የሚበረታው ከእኔ በኋላ ይመጣል። 8.እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል” የሚል ነበር።
የኢየሱስ መጠመቅና መፈተን
1፥9-11 ተጓ ምብ – ማቴ 3፥13-17፤ ሉቃ 3፥21-22
1፥12-13 ተጓ ምብ – ማቴ 4፥1-11፤ ሉቃ 4፥1-13
9.በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የገሊላ ከተማ ከሆነችው ከናዝሬት መጥቶ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ።
10.ከውሃው በሚወጣበትም ጊዜ፣ ሰማያት ተከፍተው፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ በርሱ ላይ ሲወርድ አየ፤
11.“የምወድድህ ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።
12.ወዲያውም መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድረ በዳ መራው፤
13.በሰይጣንም እየተፈተነ አርባ ቀን በምድረ በዳ ቈየ። ከአራዊት ጋራ ነበር፤ መላእክትም አገለገሉት።
የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት መመረጥ
1፥16-20 ተጓ ምብ – ማቴ 4፥18-22፤ ሉቃ 5፥2-11፤ ዮሐ 1፥35-42
14.ዮሐንስ እስር ቤት ከገባ በኋላ፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ወንጌል እየሰበከ ወደ ገሊላ ሄዶ፣
15.“ጊዜው ደርሷል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ!” እያለ ይሰብክ ነበር።
16.ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፣ ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ ዓሣ አጥማጆች ስለ ነበሩ፣ መረብ ወደ ባሕር ሲጥሉ አያቸው።
17.ኢየሱስም፣ “ተከተሉኝ፤ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው።
18.እነርሱም ወዲያውኑ መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
19.ትንሽ ዕልፍ እንዳለ፣ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን በጀልባ ሆነው መረባቸውን ሲያበጃጁ አያቸውና፣
20.ወዲያውኑ ጠራቸው። እነርሱም አባታቸውን በጀልባው ላይ ከቅጥር ሠራተኞቹ ጋራ ትተው ተከተሉት።
ኢየሱስ ርኩስ መንፈስ አስወጣ
1፥21-28 ተጓ ምብ – ሉቃ 4፥31-37
21.ከዚያም ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ፤ ኢየሱስም ወዲያው በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማር ጀመረ።
22.እንደ ጸሐፍት ሳይሆን፣ እንደ ባለሥልጣን በማስተማሩ ሕዝቡ በትምህርቱ ተደነቁ።
23.በዚያ ጊዜ በምኵራባቸው ውስጥ የነበረ ርኩስ መንፈስ ያደረበት አንድ ሰው እንዲህ በማለት ጮኸ፤
24.“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፤ ከእኛ ምን ትሻለህ? ልታጠፋን መጣህን? እኔ ማን እንደ ሆንህ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ!”
25.ኢየሱስም፣ “ጸጥ በል፤ ከርሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው።
26.ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን በኀይል ካንፈራገጠው በኋላ እየጮኸ ከርሱ ወጣ።
27.ሁሉም በመገረም፣ “ይህ ሥልጣን ያለው አዲስ ትምህርት ምንድን ነው? ርኩሳን መናፍስትን እንኳ ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል!” እያሉ እርስ በርስ ተጠያየቁ።
28.ወዲያውም ዝናው በገሊላ ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች ሁሉ ወጣ።
ኢየሱስ ብዙዎችን ፈወሰ
1፥29-31 ተጓ ምብ – ማቴ 8፥14-15፤ ሉቃ 4፥38-39
1፥32-34 ተጓ ምብ – ማቴ 8፥16-17፤ ሉቃ 4፥40-41
29.ወዲያው ከምኵራብ እንደ ወጡ፣ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋራ ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገቡ።
30.የስምዖን ዐማት በትኵሳት በሽታ ታምማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርሷም ነገሩት፤
31.ስለዚህም እርሱ ወደ ተኛችበት በመሄድ እጇን ይዞ አስነሣት፤ ትኵሳቱም ተዋት፤ ተነሥታም ታገለግላቸው ጀመር።
32.ጀንበር ከጠለቀች በኋላ፣ ምሽት ላይ የአካባቢው ሰዎች ሕመምተኞችንና በአጋንንት የተያዙትን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ።
33.የከተማዋ ሕዝብ በሙሉ በቤቱ ደጅ ላይ ተሰብስቦ ነበር።
34.እርሱም በተለያየ በሽታ የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፤ ብዙ አጋንንትም አወጣ፤ ነገር ግን አጋንንቱ የኢየሱስን ማንነት ያውቁ ስለ ነበር እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።
ኢየሱስ በገለልተኛ ስፍራ ጸለየ
1፥35-38 ተጓ ምብ – ሉቃ 4፥42-43
35.ማለዳም ገና ጎሕ ሳይቀድድ፣ ኢየሱስ ተነሥቶ ከቤት ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ ይጸልይ ጀመር።
36.ስምዖንና ባልደረቦቹም ተከትለው ይፈልጉት ነበር፤
37.ባገኙትም ጊዜ፣ “ሰው ሁሉ ይፈልግሃል!” አሉት።
38.እርሱም፣ “ከዚህ ተነሥተን በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ፤ እዚያም ልስበክ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና” አላቸው።
39.ስለዚህ በምኵራቦቻቸው እየሰበከና አጋንንትን በማስወጣት በመላዋ ገሊላ ይዘዋወር ጀመር።
ኢየሱስ ለምጻሙን ሰው አነጻ
1፥40-44 ተጓ ምብ – ማቴ 8፥2-4፤ ሉቃ 5፥12-14
40.አንድ ለምጻም ወደ እርሱ ቀርቦ ከፊቱ በመንበርከክ፣ “ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ለመነው።
41.ኢየሱስም ለሰውየው በመራራት እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ!” አለው።
42.እርሱም ወዲያው ከለምጹ ነጻ፤ ከበሽታውም ተፈወሰ።
43.ኢየሱስም ሰውየውን አጥብቆ በማስጠንቀቅ እንዲህ ሲል አሰናበተው፤
44.“ለማንም አንድ ነገር እንኳ እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ምስክር እንዲሆናቸው ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለ መንጻትህም ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ” አለው።
45.ሰውየው ግን በሄደበት ሁሉ ነገሩን በሰፊው አወራ፤ ወሬውንም አሠራጨ። በዚህ ምክንያት ኢየሱስ ወደ ማንኛውም ከተማ በግልጽ መግባት አልተቻለውም፤ ከዚህም የተነሣ ከከተማ ውጭ በሚገኙ ምድረ በዳዎች መኖር ጀመረ፤ ሰዎች ግን ከየአቅጣጫው እርሱ ወዳለበት መምጣት አላቋረጡም።